አመስግን ወዳጄ

አመስግን

ፈጣሪህ የለገሰህ ፀጋዎች ከሁሉም አቅጣጫ እንደከበቡህ አስተውል። ጤና፣ ልብስ፣ ምግብ፣ አየር፣ ውሀ… በምድር የተፈጠሩት ላንተ ነው። ነገር ግን ዋጋ አትሰጣቸውም። ከምንም አትቆጥራቸውም።

ህይወት የሰጠችህን ነገሮች ሁሉ ትቋደሳለህ ። ነገር ግን አይገባህም።

አንተ ተስተካክለው
የተቀመጡ ሁለት አይኖች፣ ሁለት እጆች፣ ሁለት እግሮች፣ ምላስ እና ጥርስ አለህ። ሥራቸውን በአግባቡ የሚከውኑ ሁለት ኩላሊቶች፣ ሁለት ሳንባዎች፣ ልብ እና ጉበት አለህ። ጤነኛ አእምሮ አለህ።
አንተ በሚገባ ተኝተህ ስታድር ብዙዎች በህመም ወይም በጭንቀት እየተሰቃዩ እንቅልፍ አጥተው ያድራሉ። አንተ በጣፋጭ ምግቦች እና በቀዝቃዛ ውሀ ሆድህን ስትሞላ
በበሽታ ምክኒያት ጥሩ የመብላት እና የመጠጣት ደስታ የራቃቸው ብዙዎች ናቸው።
እግር ባይኖረኝ ብለህ አስበህ ታውቃለህ?የማየት እና የመስማት ችሎታህን አስበው።ጤነኛ አእምሮህን ተመልከትና የአእምሮ ህሙማንን ሁኔታ አስተውል።ጥሩ የሰውነት ቆዳህን ተመልከትና ከቆደ በሽታ የጠበቀህን ፈጣሪህን አመስግን።
እስቲ ልጠይቅህ።የመስማት እና የማየት ችሎታህን እንጦጦ ተራራ የሚያህል ክብደት ባለው ወርቅ ትሸጠዋለህ? የመናገር ችሎታህንስ በትልቅ ህንፃ ትለውጠዋለህ?በርካታ ስጦታዎች ተሰጥተውሃል። አንተ ግን አሁንም ልብህ ተሽጓል።ትኩስ ዳቦ፣ ቀዝቃዛ ውሀ፣ ንፁህ አየር፣ ጤና፣ ሠላማዊ እንቅልፍ… አለህ።ቢሆንም ልብህ እንዳዘነና እንተከዝክ ነው።የሌለህን በማሰብ ተጠምደሃል።አሁንም በርካታ ንብረት የምታፈራበትና ታሪክ የምትሰራበት ቁልፍ እጅህ ላይ ነው።ራስህን፣ ቤተሰብህን፣ ጓደኞችህን፣ በዙሪያህ ያለውን ዓለም አስተውል። ባለሀብት ነህ።

አስብ እና አመስግን።


Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.